በትምህርት ተቋማት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ክበባትን በማቋቋምና ወደ ስራ በማስገባት በስነ ምግባር የተመሰገነ ትውልድን ለማፍራትና የትምህርት ተቋማት በጀት በአግባቡ ለመጠቀም እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡
ለዞን፣ ለመምህራን ትምህርት ኮሌጆችና ለወረዳ የስነ ምግባር መኮንን ፎካሎች በትምህርት ቤቶች የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ክበባት፣ ስነ ምግባር የተላበሰ ትውልድ ስለመቅረጽና የትምህርት ቤቶችን ሃብትና ንብረት በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትምህርት ቤቶች ከውስጥ ገቢ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ለፍተሃዊነትና ከተለያዩ ምንጮች የሚያገኙትን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባቸው አመልክተዋል፡፡ በጀቱ በአግባቡ ለታለመለት አላማ መዋሉን የትምህርት ቤት የስነ ምግባር ክበባትና የስነ ምግባር መኮንን ፎካሎች በሃላፊነት ስሜት ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
 
በመልካም ስነምግባር የታነፁ ዜጎችን ለማፍራት የስነ ምግባር ክበባት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የትምህርት ተቋማት ክበቡን አቋቁሞ ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ወደ ተግባር እንዲገቡ አቶ ጌታቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ኮሚሽነር አቶ ሀብታሙ ሞገስ ኮምሽኑ የትምህርት ተቋማት ሃብትና ንብረት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል፣ ትምህርት ቤቶች በእውቀትና ክህሎቱ ብቁ የሆነ ትውልድ ከማፍራት በተጨማሪ ስነ ምግባር የተላበሰ ዜጋ እንዲያፈሩ ለማስቻል ኮሚሽኑ ከአጋር አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራና ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባር መኮንን የሆኑት አቶ ጉባይ ካህሌው ባለፈው አመት በተደረገው ክትትል ከ498 ሽህ ብር በላይ ያለአግባብ የባከነ የትምህርት ተቋማት ሃብት ማስመለስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
በአሸባሪው የህወሓት ቡድንና ወራሪው የትግራይ ሃይል የተዘረፉና የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እኔም የድርሻዬን እወጣለሁ!!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና የዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *