በሽብርተኛው የህወሃት ቡድን እጇን በጥይት የተመታችው ተማሪ በሰዎች እገዛ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን እየወሰደች ነው።
—————————————
ወራሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጦርነት እጇን በጥይት ተመታ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ከህመሟ ሳታገግም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰደች ነው።
የኮምቦልቻ መሰናዶ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ቃልኪዳን ተኮላ ግራ እጇን በጥይት ተመትታ ጉዳት የደረሰባት ህዳር 16 ቀን2014ዓ.ም.ነበር።
ተማሪዋ ግራ እጇን በጥይት የተመታች ቢሆንም የቀኝ ነርቯም ስለተነካ ቀኝ እጇም ስለማይሰራ ለትምህርት ቤቱ አመልክታ እሷ ፈተናውን እያነበበችና ሰዎች እየፃፉላት ፈተናውን እየወሰደች ነው።
ተማሪ ቃል ኪዳን መምህራኖቿ ከህመምሽ አገግመሽ ሰኔ ላይ ትፈተኛለሽ ቢሏትም ‘ወደፊት የእጄ ሁኔታ አይታወቅም፣ ቀዶ ጥገናም ሊያስፈልገኝ ይችላል፣ ብዙ ጊዜ ከምጠብቅ ህመሜን ችዬ ብፈተንና ህክምናው ላይ ባተኩር ይሻላል’ በሚል ፈተናውን መውሰዷን አስረድታለች።
ተማሪዋ አባቷ በህይወት እንደሌሉና ከአቅመ ደካማ እናቷ ጋር እንደምትኖር የህክምና አገልግሎት ለማግኘትም አቅም እንደሌላት ገልጻ ድጋፍ እንዲደረግላትም ጠይቃለች።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ በቀለ ወርቁ በበኩላቸው በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳችውንና ሁለቱንም እጆቿን ያጣችውን ተማሪ ቃል ኪዳን ተኮላ ትምህርት ቤቱ ፈታኝ በመመደብ ፈተናውን እንድትወስድ ማድረጉን ተናግረዋል።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *