ማስታወቂያ
በ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ለወሰዱና አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የማመልከቻ መስፈርቶች
1. አካል ጉዳተኛ ተማሪ:- የትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና የተጎዳውን አካል ሙሉ ገጽታ የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ
2. መስማት የተሳናቸው እና የማየት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች :- የትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና የማየት ወይም የመስማት Range የምርመራ ውጤት የሚያሳይ የህክምና ማስረጃ
3. ልዩልዩ የጤና ችግር ያለባቸው ተማሪዎች:- የትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና በጤና ተቋማት ሜዲካል ዳይሬክተር የተረጋገጠ, ሶስት ሀኪም የፈረመበት የህክምና ማስረጃ
4. የሚያጠቡ እናት ተማሪዎች;- የትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወለዱበት የጤና ተቋም የክትባት ካርድ
5. የተመሳሳይ ጾታ መንትዮች:- የትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወሳኝኩነት የተገኘ የልደትካርድ ማስረጃ
ማመልከቻው በሚከተለው ማስተግበሪያ አማካኝነት የሚሞላ ይሆናል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse