ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያ መብት ከአማራ ልማት ማኅበር ጋር በመተባበር በሐይቅ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልሶ የመገንባት ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ።
በአሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የሐይቅ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገኝበታል።
የግሎባል አሊያንስ መሥራች እና ኀላፊ አርቲስት ታማኝ በየነ እንዲሁም የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፋንታ በአካል ተገኝተው ትምህርት ቤቱን የጎበኙ ሲሆን የተጎዳውን በተሻለ መንገድ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በትምህርት ቤቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው ያሉት አርቲስት ታማኝ በየነ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እርብርብ እዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሐይቅ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አራት ብሎኮች ደረጃቸውን የጠበቁ ክፍሎች እደሚሠሩ የገለፁት የአልማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፋንታ በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች የወደሙ የጤና ተቋማት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ጥገና ይሠራሉ ብለዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን በበኩላቸው በቬጋስ እና አትላንታ የኢትዮጵያ ማኅበር ግሎባል አሊያንስ ከአልማ ጋር በመተባበር ትምህርትቤቱን ለመሥራት በመነሳሳታቸው ምስጋና ማቅረባቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *