የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂደ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር የ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል

በግምገማው የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል፣  የጎልማሶችና የልዩ ፍላጎት ትምህርትን ማሳደግ በቀጣይ በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ቢሮው የመምህራንን ስምሪት ችግሮች ለመፍታት ይሰራል፣ ከአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ጋር በተያያዘ መምህራን በክረምት ስልጠና እንዲያገኙና  አዳዲስ የትምህርት ቤት አመራሮችንም በማሰልጠን ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚደረግ ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም መምህራን የተከታታይ የሙያ ማሻሻያን እንዲተገብሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባም ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ ገልጸዋል፡፡

ቢሮው ለግል ትምህርት ቤቶችም ድጋፍና ክትትል እንደሚያደረግም ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በክልሉ በከፈተው ወረራ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ጉዳቶች አድርሷል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተዘረፉና የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡  ከመልሶ ግንባታው ጎን ለጎን መደበኛ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡

የትምህርት ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጅ በማስደግፍ ለማዘመን አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የወደሙና የተዘረፉ የትምህርት ተቋሞቻችንን መልሶ ለመገንባት አቅምዎ የፈቀደውን የገንዘብ መጠን ወደ 9222 በአጭር የጽሁፍ መልእክት ይላኩ፡፡

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

 

ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w

በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/

በቴሌግራም https://t.me/anrse

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *