በእውቀት፣በአመለካከትና በክህሎት ከፍያለ የሰው ሀብት በማልማት ለሀገር ልማት ዋስትና የሆነና ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠር ይገባል ተባለ፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ዘመኑን የ6 ወር እቅድ አፈፃጸም የክልል፣የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በፍ/ሰላም ከተማ የግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡
በግምገማ መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) እንደገለጹት ትምህርት መታጠፊያ ቦታችን መሆኑን አውቀን ልሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የህዝባችን ከፍታ የሚወሰነው በምንሰራው የትምህርት ስራ ነው፡፡ ትምህርትን ህዝባዊ በማድረግና በቁጭት በመስራት ለክልሉና ለሀገራችን ብቁ ዜጋ የማፍራት ተልኳችን ለማሳካት ትምህርት እንዴት ውሎ እንዳደረ መከታተል የሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
የተለወጠ ማህበረሰብ ማየት የሚቻለው ህፃናት ላይ በምንሰራው ልክ በመሆኑ የህፃናት እጣ ፈንታ የተወሰነው ደግሞ በዚህ ዘመን ባሉ አመራሮችና የትምህርት ባለሙያዎች በመሆኑ እያንዳንዷን ቀን በአግባቡ ልንጠቀም ይገባል ተብሏል፡፡
ተሳታፊዎች በበኩላቸው በትምህርት ስራችን ከወደቅን በሁሉም የልማት ስራዎቻችን ላይ ያለው ተጽኖ ከባድ በመሆኑ የታቀዱት የትምህርት ስራዎች እንዲሳኩ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ማህበረሰባችን በትምህርት ካልተለወጠ አጠቃላይ እድገትና ለውጥ አይታሰብም በመሆኑም ትምህርት ዋናው የትኩረት ስራችን ሊሆን ይገባል፡፡
ዛሬን ዋጋ ከፍለን ነገን እንገንባ በሚል መሪ ሀሳብ የተስማሙት የግምገማው ተሳታፊዎች ትምህርት ሰፊ ሀብትና አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ ያለንን ሙሉ አቅም አሟጠን በመጠቀም የአማራን ህዝብ ከፍታ ለማረጋገጥ ከህዝባችን ጋር ዛሬ ዋጋ እንከፍላለን ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡
ለትምህርት ስራችን ቁልፍ የሆኑትን መምህራንንና የትምህርት አመራሮችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ቢሮው እስካሁን የሰራቸውንና በቀጠይ ሊሰራቸው ያቀዳቸው ተግባራትም አድናቆት ተችሯቸዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሁሉም ዞኖችና በከተማ አስተዳደሮች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ያለመውን ራዕይ ለማሳካት በውይይቱ የተገኙ የዞን አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ሀሳቡን በመቀበል አዳሪ ትምህርት ቤት ለመክፈት ቃል ገብተዋል፡፡
የጎልማሳው ትምህርት ትኩረት ያልተሰጠውና በቀጣይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ባለውለታችን የሆነውንና በችግር ጊዜ ኢትዮጵያን የሚመግበው አርሶ አደሩን ማንበብና መፃፍ እንዲችል ካላደረግነውና ካላዘመንነው እድገት አይታሰብም፡፡ በቀጣይ የጎልማሶችን ትምህርት ውጤታማ ማድረግ ለህዝባችን ለውጥ ያለው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ተብሏል፡፡
የትምህርት ቢሮ የ6 ወር እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ የጋራ ራዕይ የተሰነቀበትና ዛሬን ዋጋ ከፍለን ነገን እንገንባ እንዲሁም ትምህርት መጣጠፊያ ቦታችን ሊሆን ይገባል የሚሉ ታላለቅ ሀሳቦች የውይይቱ ዋና ነጥቦች ነበሩ፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/Backup dec 2021/Backup dec 2021/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *