“አማራ ልማት ማኅበር ትምህርት ቤት መንደራችን ገንብቶ ስላስረከበን ውጣ ውረዳችንን አስቀርቶልናል” በማቻከል ወረዳ የሐሙሲት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች
 በምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ያስገነባውን ባለ አንድ ፎቅ የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቋል።
ካሁን ቀደም በማቻከል ወረዳ የሐሙሲት አካባቢ ተማሪዎች የኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ከ30 ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝና ከወላጅ ርቀው በሌላ ስፍራ ለመማር ይገደዱ ነበር።
የቤት ኪራይ እና የትራንስፖርት ወጭ ለተማሪ ወላጆች ፈተና ኾኖ ቆይቷል። በርካታ ተማሪዎች ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርትን ለመቀጠል ፈታኝ እንደነበር ወላጆችና ተማሪዎች ይናገራሉ።
ዛሬ ላይ ግን የትላንት ትምህርት ፍለጋ የኪሎ ሜትሮች ጉዞና እንግልት የወላጆች አቅምን የፈተነ የትምህርት ወጭ መቋጫ ሊያገኝ አማራ ልማት ማኅበር ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ያስገነባው ባለ አንድ ፎቅ ትምህርት ቤት እፎይታን ፈጥሮልናል ብለዋል።
“አማራ ልማት ማኅበር ትምህርት ቤት መንደራችን ገንብቶ ስላስረከበን ውጣ ውረዳችንን አስቀርቶልናል” ነው ያሉት ተማሪዎችና ወላጆች
የአማራ ልማት ማኅበር በክልሉ የትምህርት ቤቶችን የጥራት ደረጃ ከ16 ወደ 50 በመቶ ለማድረስ እየሠራ ይገኛል። ባለፉት ኹለት ዓመታትም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማትና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን ከኅብረተሰቡ በሰበሰበው ገቢ ገንብቶ ማስረከቡን በአማራ ልማት ማኅበር የምሥራቅ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም አንዳርጌ ተናግረዋል።
አልማ በማቻከል ወረዳ ያስገነባው የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 174 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል።
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
(አሚኮ)
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *