የጎልማሶች ትምህርትን ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ፡፡
———————————————
የጎልማሶች ትምህርትን በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ እና ለመደገፍ የሚያስችል የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር መመስረቱ ተገልጿል፡፡
ዘርፉን አሁን ካለበት ችግር ለማላቀቅ ያለመ የዘርፉ ባለሙያዎች ማህበር በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የመመስረቻ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩም የጎልማሶችና የሕይወት-ዘመን ትምህርት እና ማኅበረሰብ ልማት (ጎሕትማል) ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ማህበሩ ተመስርቷል፡፡
የሙያ ማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የሙያ ማህበሩን በቀጣይ የሚመሩ አመራሮችም ምርጫ ተካሂዷል፡፡
በምስረታ ጉባኤው ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ የተማረ የሰው ሃይል ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡
MOE
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *