የትምህርት ተቋማት በስራ እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ለአካባቢ ደህንነትና የማህበራዊ ጥበቃ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ማሻሻያ ለፍትሃዊነት ፕሮግራም የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ደባሱ ያየህ የትምህርት ተቋማት ግንባታ፣ የማስፋፊያ ስራና የቤተ ሙከራ አጠቃቀም ከአካባቢ ብክለት የጸዱና ማህበራዊ ድህንነታቸው የተረጋገጠ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች በሚገነቡበት ወቅት የአካባቢ ብክለትና ማህበራዊ ደህንነት ስጋት እንዳያሳድሩ በማቀድ ከአካባቢ ጠበቃ ባለሙያዎች ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ከየአካባቢው ህብረተሰብ ባህል እሴትና ቅርስ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማስቻል በተዘጋጀው እቅድ ላይ ከየአካባቢው ህብረተሰብ ጋር የጋራ መግባባት እንደሚያስፈልግም አቶ ደባስ አመላክተዋል፡፡
የሚገነቡ የመጸዳጃ ቤቶች የከርሰ ምድርና የመጠጥ ውሃን እንዳይበክሉ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
መምህራንና ተማሪዎች የቤተ ሙከራ ስራዎችን በሚሰሩበት ወቅት በራሳቸውና በአካባቢያቸው ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ባለሙያው መክረዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ተቋማት ለአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡ ለትምህርት ቤት አመራሮች ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *