ለርእሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የአእምሮ ጤና፣የስነ ልቦና ማህበራዊ ድጋፍ ስልጠና ተሰጠ
አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአማራ ክልል በወረራ በያዘበት ወቅት በመምህራን በተማሪዎችና በአጠቃላይ በህብረተሰቡ ላይ በርካታ በደሎችን ማድረሱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ተከትሎም በመምህራን በተማሪዎችና በመላ ህብረተሰቡ ላይ የስነ ልቦና ጫና አሳድሯል፡፡
ይህን የስነ ልቦና ጫና ለመፍታት የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም ለመምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የአእምሮ ጤና፣ ስነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ስልጠና በደሴ ከተማ ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን ሲሰጡ ያገኘናቸው አቶ ደማሙ አደሬ ስልጠናው ተማሪዎችና ወላጆች የደረሰባቸውን የስነ ልቦና ስብራት መጠገን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሰልጣኞች በስልጠናው በጦርነቱ ምክንያት በመምህራንና ተማሪዎች ላይ የደረሰውን የስነ ልቦና ጫና በመቋቋም የመማር ማስተማሩን ስራ ለማከናወን የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዶሰን አቢ ስልጠናውን የወሰዱ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የየትምህር ቤቶቻቸውን መምህራን፣ ተማሪዎቻቸውንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ማሰልጠን እንዳለባቸው አሳሳበዋል፡፡
መምህራን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የመማር ማስተማሩን ስራ በላቀ ውጤታማነት መፈጸም እንዲችሉ ስልጠናውን በቀጣይነትም መሰጠቱ እንደሚቀጥል አቶ ወንዶሰን አመላክተዋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse