የኦ ክፍል ትምህርትን በኢንስፔክሽን ለመለካት የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ::
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለ ኦ ክፍል መምህራን የመማር ማስተማርን የተመለከቱ ስልጠናዎች በተከታታይነት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ስልጠናው አዳዲስ የመማር ማስተማር ዘዴዎችና አተገባበሮች የተካተቱበት በመሆኑ በኢንስፔክሽን ለመለካት ለኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በትምህርት ቢሮ የኢንስፔክሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች የኦ ክፍል ትምህርትን በኢንስፔክሽን ለመለካት የሚያስችል ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጥቷል፡፡
ለኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ስልጠናው በመሰጠቱ ለኦ ክፍል ትምህርት ቤቶች ደረጃ ለመመደብ እንደሚያስችላቸው ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡
የኦ ክፍል መምህራን በተከታታይነት የወሰዱት ስልጠና በትምህርት ቤቶቻቸው ያመጣውን ለውጥ ለመለካት የኦ ክፍል ትምህርት ቤቶችን ኢንስፔክሽን በመስራት ደረጃቸውን ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን አቶ ብርሃኑ አመላክተዋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *