በጎንደር ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ከ250 ሚሊየን ብር ከተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች ለመስብስብ እየተስራ መሆኑ ተጠቆመ።
የአማራ ልማት ማህበር አልማ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በንዘብና በግብዓት አቅርቦት በመደገፍ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ህብረተስቡና ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ በማድረግ በከተማዋ የትምህርት ልማት አሻራቸውን እንዲያስቀምጡም ጥሪ ቀርቧል።
የጎንደርና አካባቢው የአማራ ልማት ማህበርና የጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ታዋቂ ግለስቦች ፣የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮችና አጋር አካላት የተሳተፉበት የትምህርት ስራዎች የንቅናቄ የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።
የንቅናቄ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ እንደገለፁት አልማ ለክልላችን ህዝብ በርካታ የልማት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።
ማህበሩ የለውጥ ዕቅድ አቅዶ በትምህርት ዘርፍ በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳደግ ረገድ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።
ማህበሩ እያከናወናቸው ያሉ የትምህርት ስራዎችን በዕቅዱ መስረት ማሳካት እንዲችል ከማህበሩ አባላት ፣ከለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ጋን በጠጠር ይደገፋል ያሉት ምክትል ከንቲባው የመምሪያና የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣የግል ትቋማት ፣ረጅ ድርጅቶችና ግለስቦች የአልማ የከተማዋን ልማት ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት በገንዘብና በውቀት መደገፍ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጎንደርና አካባቢው አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ አለህኝ ጓዴ ደግሞ የማህበሩን አመስራረት ታሪካዊ ዳራና ማህበሩ አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ አጠቃላይ መረጃና የንቅናቄ መድረኩን የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።
ማህበሩ በጎንደርና አካባቢው 369 ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ታቅዶ 101 ፕሮጀክቶች ከመስረት እስከ ማጠናቀቂያ ደረጃ የደረሱ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በጎንደር ከተማ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የ10 ትምህርት ቤቶችን ግንባታ መጀመሩንም ገልፀዋል።
ማህበሩ በጎንደርና አካባቢው ከ262 ሚሊየን ብር በላይ ለመስብስብ አቅዶ እየስራ ሲሆን እስካሁንም ከ72 ሚሊየን ብር መስብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
በጎንደር ከተማ በአልማ 56 ሚላየን ብር ለመስብስብ ታቅዶ እየተስራ መሆኑን ገልፀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ደግሞ አሁን ላይ 76 የግልና የመንግስት ትምህርት ተቋማትን ደረጃ በማሳድግ ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ለመፍጠር እየትስራ ሲሆን በቀጣይ ዓመት
ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ሞዴል በማድረግ ደረጃቸውን ለማደግ በአልማ አስተባባሪነት 250 ሚሊየን ብር ለመስብሰብ የንቅናቄ ዕቅድ መጀመሩን
ገልፀዋል።
አልማ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል ከፍ እያበረከተ ሲሆን ህብረተስቡ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ በማድረግ ለትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሳደግ ስራ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ግርማቸው መላኩ ማህበሩ ሀብት ከማስባስብ ጎን ለጎን
አባላትን ማፍራትና በማህበሩ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በመከታተልና የሀብት ብክነት እንዳይፈጠር መስራት ይገባል ሲል አስተያየቱን ስጥቷል።
የአማራ ክልል የተማሪ ወላጅ ህብረት ፕሬዝዳንት አቶ አዱኛ እሽቴ ደግሞ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሳደግ ተግባር የሚያበረታታ ነው።ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል።ተግባሩን ሁላችንም በቁርጠኝነት ልንስራ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ስጥተዋል።
የአማራ ልማት ማህበር አልማ በ1983 ዓ.ም የተቋቋመ ማህበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት 4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላት አሉት።
ዘገባው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በቴሌግራም https://t.me/anrse