ለቅድመ አንደኛ ደረጃ የመፃፍትና የመማርያ ቁሳቁስ (ሜንቶሶሪ አገልግሎት የሚውሉ) ግብዓቶች ስጦታ ተደረገ
አሜሪካዉያን ባለትዳሮች Emory Patterson እና charlotte Patterson ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ መፀሐፍትና መማሪያ ቁሳቁሶችን ለዞኑ ት/ም መምሪያ በስጦታ አበረከቱ፡፡
ስጦታዉን በቦታዉ ተገኝተዉ የተቀበሉት የዋግ ኽምራ ብ/ሰብ አስ/ር ትም/ት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ሞገስ ስጦታውን በማመስገን የተረከቡ ሲሆን የሚከተለውንም ብለዋል፡-
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የትም/ት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ ሊከናወን የሚገባ የትም/ት ፕሮግራም መሆኑ ታምኖበት በግልና በመንግስት የ1ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች በስፋት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም የህፃናት ትም/ት ለሁለንተናዊ እድገታቸው አስፈላጊ የሆነ እና ለቀጣዩ የመደበኛ ትም/ት አቀባበል የሚያዘጋጅ የትም/ት መሰረት ነው፡፡ ሆኖም ግን አሁን ካለው የሃብት ውስንነት አኳያ አስፈላጊና በቂ የሆኑ የትም/ት ግብዓቶችን ማሟላት ላይ ውስንነቶች ይስተዋላሉ፤ ይህ ደግሞ ለትም/ት ጥራት የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖን አሳድሯል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት ከመንግስት ባሻገር የአከባቢው ማህበረሰብ፣ ለጋሽ ድርጅቶችና ግለሰቦችን እንዲሁም የሌሎች አካላትን ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም በስጦታ የተገኘውን የመማሪያ ቁሳቁሶች በየትም/ት ተቋማቱ በማሰራጨት የአፈፃፀም ሂደቱን የመምሪያው የትም/ት ባለሙያዎችና ልገሳ ባደረጉት ጥንዶች ተወካይ በወ/ሮ ሙሉነሽ በላይ አማካኝነት የሚፈፀም ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም ይህ ሃብት ወደ ትም/ት መምሪያዉ ገቢ እንዲሆን ያልተቋረጠ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩቱን የትም/ት መምሪያዉ ባልደራ አቶ ካሳ ሺበሺና ባለቤታቸዉ ወ/ሮ ሙሉነሽ በላይ ላደረጉት አስተዋጾኦ አመሰግናዋል ፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
ምንጭ የዋግ ህምራ ዞን ትምህርት መምሪያ
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse