ማስታወቂያ
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጠይቃለን፡፡
1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *