በህጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት የወላጆች፣ የማህበረሰቡና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራሞች አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በቀዳሚ ልጅነት ጊዜያቸው ጥሩ እንክብካቤና ትምህርት ያገኙ ህጻናት በመጀመሪያ ደረጃ ፣ በሁለተኛ ደረጃና በዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው ውጤታማ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ሕጻናትን ለመደበኛ ትምህርት በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው ደግሞ የቅድመ መደበኛ ትምህርት፣ የወላጆችና የማህበረሰቡ ድጋፍ መሆኑን ልዩ ልዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
የኖቬል ተሸላሚ የሆነው ፕሮፌሰር ጄምስ ሄክማን እና ሌሎችም “በሰው ልጆች ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ በሰው ኃይል መልማት ላይ የእድሜ ልክ የተጠራቀመ ውጤት የሚያመጣ” ነው በማለት ገልጸውታል፣
ፕሮፌሰር ጄምስ ሄክማን በህጻናት ላይ በመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የአንድ ዶላር ኢንቨስትመንት በልጆት የኋላ ወይም የስራ ዘመን ላይ $7 እስከ $9 የሚደርስ ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦነት ያበረክታሉ በሚል አስቀምጦታል፡፡
ሕጻናት የዓእምሮ፣ የአካልና የማህበራዊ እድገታቸው የሚወሰንበትና የቅድመ መደበኛ ትምህርትን በሚያገኙበት ጊዜአት በመሆኑ በመደበኛው ትምህርት ለሚኖራቸው ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራምን በማስፋፋት ውጤታማ ይሆን ዘንድ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው፡፡
ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስታንዳርድና ሥርዓተ ትምህርትም ስራ ላይ በማዋል የህፃናትን አካላዊ ፣ አእምሯዊ ፣ ማህበራዊ እና ስሜታዊ እድገቶችን በማዳበር ለመደበኛ የትምህርት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዘርፉ ውጤታማነት ትኩረት በመስጠት የቅድመ መደበኛ ትምህርት በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፋ በማድረግና ለመምህራንና ለትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች ስልጠና በመስጠት፣በመምህራን ኮሌጆች መምህራንን በማሰልጠን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግብአቶችን በማሟላት ፕሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራሙን በኢንስፔክሽን በመለካት ደረጃውን ለማሻሻል ለኢንስፔክሽን ባሙያዎች ከሰሞኑ በተሰጠው ስልጠና እድሜአቸው ከ4-6 ዓመት ለሆኑ ህፃናት የሚሰጠው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ውጤታማ መሆኑ ለቀጣይ የህፃናት ውጤታማነት ሚናው የጎላ በመሆኑ ወላጆችና ህብረተሰቡ በህፃናት እድገትና እንክብካቤ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse