የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪ መቀመጫ ወንበሮችን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች እያሰራጨ ነው፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ35 ሚሊዬን ብር ወጭ ያሰራቸውን የተማሪ መቀመጫ ወንበሮችን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በማሰራጨት ላይ መሆኑን የትምህርት ግብዓቶች ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይርሳው ብርሃኔ ገልጸዋል፡፡
ቢሮው ከ12ሽህ በላይ ወንበሮችን በማሰራት ዞኖች በጦርነቱ የደረሰባቸውን ጉዳትና የተማሪ ቁጥራቸውን ታሳቢ በማድረግ ደልድሎ ስርጭት እያከናወነ መሆኑን አቶ ይርሳው ተናግረዋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *