የባላምባራሳ አበጋዝ ሞላ ልጆች እና ቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአንድ ሚሊየን ብር የመማሪያ ቁሳቁስ ለኩታበር 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ድጋፍ አደረጉ።
የባላምባራሳ አበጋዝ ሞላ ልጆች እና ቤተሰቦቻቸው ባቋቋሙት ግሎባል ኢዱኬሽን ፋውንደሽን ግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኝነት የተለያዪ ቁሳቁሶችን ለቀድሞ ት/ቤታቸው 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ድጋፍ አድርገዋል።
በርክክቡ ወቅት የባላምባራስ አበጋዝ ሞላ ልጆች ፣የወረዳው ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አበባው ፣የትም/ት ጽ/ቤት ኋላፊዎች ሌሎች የወረዳው አመራሮች ፣የትም/ቤቱ የወ.መ.ህ አባላት ፣ርዕሳነ መምህሮች ፣መምህሮች እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ለትም/ቤቱ ግብዓት የሚሆኑ 2 አውቶማቲክ ጀነሬተር ፣ ዘመናዊ ፎቶ ኮፒ ማሽን ፣10 ኮምፒውተር፣600 በላይ አጋዥ መፅሀፍትና የስፖርት ሙሉ ትጥቅ ከነኳሱ ለኩታበር ሁለተኛ ድርጅት ት/ቤት አበርክተዋል።
የባላምባራስ አበጋዝ ሞላ ልጅች መካከል 84 ሀገራትን በመዘዋወር ረጅም ልምድ ያካበቱ እና የተለያዪ ዩንቨርስቲዎች በማስተማር እና የተለያዪ ምርምሮችን የሰሩ የተከበሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ አበጋዝ የተገኙ ሲሆን በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት የተማርንበትን ት/ቤት ና ማህበረሰብ የደረሰበት ጉዳት እንደተሰማን ህመሙ እንዳመመን ለመግለጽ እና ከጎናቹ እንደሆንን ለማሳየት ነው የመጣነው ሲሉ ተናግረዋል።በቀጣይም ላሳደገን ማህበረሰብ እና የእውቀት ማዕድ የቀሰምንበት የቀድሞ ት/ቤታችን መሰል ድጋፎች እናደርጋለን ብለዋል።
ሌላዋ የባላምባራስ አበጋዝ የመጨረሻ ልጅ ወ/ሮ ገነት አበጋዝ እንደተናገሩት አሁን ላይ የተደረገው ድጋፍ ጊዜአዊ ችግርን የሚፈታ ሲሆን በቀጣይ የተሰበሩ መስኮቶችንና በሮችን እንዲጠገኑ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። አያይዘውም በቤተሰቡ በተቋቋመ ግሎባል ኢዱኬሽናል ፋውንዴሽን መሰረት ከ2009ዓ.ም ጀምሮ ት/ቤቱ ውስጥ ለሚማሩ 10ሴት ተማሪዎችን የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
የኩታበር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዳኘ ጎበዜ እንደገለፁት ት/ቤቱ በጦርነቱ ም/ያት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደ መሆኑን ገልፀው የተደረገዉ ድጋፍ በጥናት ላይ የተመሰረተና ወቅታዊ ምላሽ የሰጠ በመሆኑ የመማር ማስተማሩን ስራ የተቃና ያደርግልናል ብለዋል። አክለውም ሁሉም የአካባቢው ተወላጅ ለት/ቤቱ የአቅሙን እንድያበረክት ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም የዛሬውን ድጋፍ ላደረጉት የባላምባራስ አበጋዝ ሞላ ቤተሰቦች እና ቀደም ሲል ኩታበሮች ነን በሚል የቴሌግራም ግሩፕ ከፍተው በማስተባበር 397 መፃሀፍትን ገዝተው ለት/ቤቱ ላስረከቡት አካላት የወረዳው ት/ት ጽ/ቤት ያዘጋጀውን የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት በወረዳው ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አበባው በኩል ተበርክቶላቸዋል።
ኩታበር ኮሙኒኬሽን
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse