“ሕዝብ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጣ ከሆነ ተሻጋሪ የኾነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
____________________________________________________________
የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በጦረነት ሥነልቦና ውስጥ ኾነው ፈተና መውሰዳቸው እንደጎዳቸው ቢሮው ገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ.ር) የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት የሥራ ኀላፊዎች፣ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጡ ከሆነ ተሻጋሪ የኾነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡
ተማሪዎች ደክመው፤ ጥረው ባጠኑት ልክ በሚያገኙት ውጤት አመኔታ ሊያሳድሩ እንደሚገባም ነው ኀላፊው ያስረዱት፡፡
መምህራንም ባስተማሩት ልክ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
የትምህርት የሥራ ኀላፊዎችም በአመራር ዘመናቸው የሠሩትን ውጤት ማየት ስለሚፈልጉ በሚመጣው ውጤት አመኔታን የማያሳድሩ ከሆነ እንደ ሀገር ችግር ሊያጋጥም ስለሚችል ችግሩ ሊፈታ ይገባል የሚል የክልሉ አቋም እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ ውጤቶችን ተንትኖ የውሳኔ ሀሳብ ካቀረበ በኋላ ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቶቹን ተንትኖ ፍትሐዊ የኾነ የመቁረጫ ነጥብ መወሰንና ግልጸኝነት የመፍጠር ኀላፊነት እንዳለበት አብራተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር እየተፈጠረ ያለውን የእምነት ማጣት ጉዳይ ግልጽ አሠራር በመዘርጋት መተማመን መፍጠር እንዳለበት ክልሉ ያምናል ብለዋል፡፡
ዶክተር ማተብ ውጤቱ ከተገለጸ በኋላ ቢሯቸው ባደረገው ግምገማ የክልሉ ተማሪዎች ውጤት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልሉ ዝቅ ያለ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡ ውጤቱ እንዲስተካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባበት ወቅት እንዲራዘም እና ጉዳዩ እንዲጣራ ለትምህርት ሚኒስቴር በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረባቸውን ዶክተር ማተብ አስታውሰዋል፡፡
ሂደቱን የሚያጣራ ግብረ ኃይልም ወደ ሚኒስቴሩ መላካቸውን አስረድተዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የክልሉ ተማሪዎች በጦርነቱ በመጎዳታቸው እና ሳይዘጋጁ በመፈተናቸው በተለየ መንገድ ጎድቷቸዋል የሚል አቋም እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
ችግሮቹን ለመፍታት በሰከነ መልኩ የተማሪዎቹንና የሕዝቡን መብት ለማስከበር መሥራት እንዳለበት ታምኖ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት፡፡
ዘገባው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *