የ2014 የትምህርት ዘመን የትምህርት መረጃ ወቅታዊና ተአማኒ እነዲሆን በጋራ ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡
===========================================
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ዘመኑን የትምህርት መረጃ ወቅታዊና ተአማኒ ለማድረግ ያግዘኛል ያለውን ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት በእንጅባራ ከተማ አካሂዷል፡፡
በትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት፣ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው አማራ ወቅታዊና ተአማኒ የትምህርት መረጃ ለውሳኔ ሰጭ አካላትና ለበጀት ምደባ ዋና መለኪያ በመሆኑ የትምህርት መረጃዎችን በጥንቃቄ ማደራጀት ይገባል ብለዋል፡፡
በትምህርት ቤት ያለው የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ ይሆን ዘንድ በጀት ወሳኝ ጉዳይ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ አለማቀፍ ተቋማትም ሆነ መንግስት ለትምህርት ስራው በጀት ለመመደብም ሆነ በትምህርት ስርአቱ ውሳኔወችን ለመወሰንና ለፖሊሲ አውጭወች ዋናው መነሻ እኛ የምናሰባስበው መረጃ በመሆኑ መረጃን ወቅታዊና ተዓማኒ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚሰበሰበው የትምህርት መረጃ ወቅታዊና ተዓማኒ እንዲሆን በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን በመረጃ አሰባሰቡ ሂደት ዙሪያ በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ሳምንታ ስልጠና እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
በልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች ትምህርት ፐሮግራም ባለፉት ዓመታት የነበረው የመረጃ ችግር በዚህ ዓመት እንዳይደገም በጥንቃቄ ሊሰራ ይገባለክ ተብሏል፡፡ ለመረጃ መሙያ የሚውሉ ቅፃቅፆችም ህትመት ተጠናቆ መላካቸው ታውቋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *