የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ውጤታማ  እንዲሆኑ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የእድገት ማእከል /ኢሲዲዲ/ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የድርጅቱ ፕሮጀክት ኦፊሰር አመለወርቅ ልመንህ  ድርጅታቸዉ አካላል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በተለያዩ ተግባራት በማገዝ ዉጤትማ እንዲሆኑ ለማስቻል በክልሉ በሚገኙ በርካታ ዞኖች እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በክልሉ የሚገኙ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ወይዘሮ አመለወርቅ አመላክተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ሁሉም ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸው፣ ትምህርት ቤት የመጡት ህጻናት በመለያ ማንዋሉ መሰረት መለየት አለመቻላቸው በልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

በትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ባለሙያ  ስንታየሁ እምሩ ሁሉም መምህራን የምልክት ቋንቋ ላይ ስልጠና ባለመውሰዳቸው በአካቶ መማር ማስተማር ሂደት ላይ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች  ትምህርቱን በአግባቡ ለመረዳት እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ማድረግ፣ ወደ ትምህርት ቤት የመጡትንም ልየታ ማድረግ፣ የልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች በአካቶ ለሚያስተምሩ መምህራንም የምልክት ቋንቋን እንዲሰለጥኑ ማደረግ እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡

የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።

በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w

በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/

በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *