የጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ፡፡
_____________________________________________
መምሪያው በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሰባሰበውን ከአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ጥሬ ገንዘብ፣ የትምህርት ግብዓቶች፣ አልባሳትና ምግብ ነክ የሆኑ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
በሰቆጣ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት መምሪያ ኋላፊ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ድጋፉ የጎንደር ከተማ ህዝብ ለዋግኸምራ ህዝብ ያለውን አጋርነት ያሳየበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዋግኸምራ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ነጋሽ ድጋፉ የዋግንና የጎንደርን ህዝብ አንድነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።
የዋግኸምራ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፋ ነጋሽ የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ በራስ ተነሳሽነት አጋርነት በማሳየት ላደረገው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በዋግ ህዝብና ህፃናት ስም አመስግነዋል፡፡ ኃላፊው በቀጣይም ግንኙነቱን በማጠናከር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *