የትምህርት መረጃዎችን ወቅታዊና ትክክለኛ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
_______________________________________________
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ11ሽ በላይ ለሚሆኑ የአፀደ ህፃናት፣ አንደኛ ደረጃ ና ለ2ኛ ደረጃ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን የትምህርት ስርዓቱን የመረጃ ችግሮች ለመቅረፍ በሚያስችሉ የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ላይ ስልጠና ሰጥቷል::
የትምህርት ልማት መረጃ አስተዳደር ባለሙያ አቶ ዘመነ አበጀ ስልጠናው ከዚህ በፊት የነበሩ የትምህርት ስርዓቱን የመረጃ ችግሮች ለይቶ በመፍታት የትምህርትን ቀጣይ ሂደትን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ የትምህርት መረጃዎች ትክክለኛና ወቅታዊ በማድረግ ለውሳኔ ሰጭ አካላት በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል ።
ስልጠና የወሰዱ ርዕሳነ መምህራን በቀጣይ ጥራት ያለውና ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብ ለትምህርት ስርዓቱ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት እንደሚያስችላቸው አቶ ዘመነ አመላክተዋል ፡፡
የስልጠናው ተሳታፊ ርዕሰ መምህር ኤፍሬም ሙሉጌታ እና ቅድስት ሰጠኝ ከዚህ በፊት የነበሩ የመረጃ አሰባሰብ ችግሮችን በመለዬት እንዲሻሻሉ መደረጉ ጥራት ያለው መረጃ ለማሰባሰብ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኞች በስልጠናው ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሰ መምህራን በመሳተፋቸው የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse