ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ የቀረበ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እየተመኘ፡፡

ቢሮው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊነቱ እና ተደራሽነቱ የተረጋገጠ ትምህርት በመስጠት በክልሉ የሰው ሃብት ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ትምህርት ቢሮው የበኩሉን ጥረት እየተወጣ ቢሆንም በተለይ በትምህርት ጥራቱ ረገድ ያሉ ችግሮች የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በጽኑ ያምናል፡፡

በተለይ የክልላችን ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆችና የትምህርት አመራሮች የትምህርት ጥራት ማነቆዎችን በመፍታት ረገድ የተለዬ ቁርጠኝነትና ትጋት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ለማሳሰብ ይወዳል፡፡

በትምህርት ቢሮው በኩል በርካታ የሰው ሃይል ማሟላት፣ የትምህርት ቁሳቁስና መሰረተ ልማት እንዲሁም የአመራር ማሻሻያዎች እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡

ለአብነት

ከትምህርት አመራር ጋር የተያያዙ የማሻሻያ ሪፎርሞች፣

ከመምህራን የስራ ስምሪት ጋር የተያያዙ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎች፣

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያዎች፡_ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሃፍት ዝግጅትና የሙከራ ትግበራዎች ተጠናቅቀው በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ ለመሸጋገር የመጽሃፍት ህትመት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

የትምህርት ቤት ግንባታዎችን በተመለከተ በ2014 ዓ.ም

በክልሉ መንግስት በጀት አስራ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ናቸው፡፡

በአፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል አስር ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በባህር ዳር ከተማ አንድ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትና በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው የክልሉ አካባቢዎች መቶ ሰባ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡

በንጋት ኮርፖሬት ስር በሚገኘው ዳሽን ቢራ አማካኝነት በጎንደር ከተማ አንድ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት ስምምነት ላይ ተደርሷል

በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የዩኒቨሪሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ጋር ተያይዞ የተማሪዎችን ጥያቄ በሰከነና በአስተዋይነት አካሄድ ሀገራዊ ምላሽ እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡

በምላሹም ለሁሉም የክልላችን ተማሪዎች የውሳኔው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በጦርነቱ አካባቢ ማለት እንደ አማራ ክልል ሁሉንም የክልሉ አካባቢዎች የሚያካትት ነው፡፡

በመሆኑም በቀጣይ የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ የክልላችን ተማሪዎችን በማዘጋጀቱ ሂደት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎችም የተሰጣችሁን ሃገራዊ እድል በተለዬ ቁርጠኝነት በመዘጋጀት የክልላችሁና የሃገራችሁ ኩራት መሆናችሁን እንድታስመሰክሩ ቢሮው በአጽናኦት እያስገነዘበ በፈተና ዝግጅታሁ ሁሉ የሚያስፈልጋቹን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብና የበረከት እንዲሆንላችሁ በድጋሚ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም

ዶክተር ማተብ ታፈረ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *