በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የካቲት 13/2016 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ የፀጥታ ችግር ትምህርት ያልጀመሩ አካባቢዎችን ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ከሚመለከታቸው የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በባህርዳር ከተማ ሰሞኑን ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንት አደመ እንደተናገሩት የትውልድ ቅብብሎሽ ለማስቀጠል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሂደት አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም በየካቲት ወር የተማሪ ምዝገባ በማካሄድ ትምህርት ማስጀመር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ እስካሁን የባከነውን ጊዜ ግምት ውስጥ ያስገባ የትምህርት ካሌንደር መዘጋጀቱን የተናገሩት ኃላፊው የትውልድ ቅብብሎሹ እንዳይቋረጥ ሁሉም አካላት ህፃናት እንዲማሩ ድጋፍ እንዲያደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ የተሳተፉት የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች በፀጥታ ችግሩ ምክንያት የትምህርት ስርዓቱን ክፉኛ መጎዳቱን ተናግረዋል፡፡ አሁንም ባለው ጊዜ የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት የመንግስትና የባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተወያዮቹ ገልፀዋል፡፡
“ትምህርት ለትውልድ”
  
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *