=====================
የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ከደብረታቦር ዩኒቨርስቲ እና ከማህበረ ቅዱሳን ደብረታቦር ማዕከል ጋር በመተባበር ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዪንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የሥነ-ልቦና ግንባታ ሥልጠና መስጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ እየበሩ አዕምሮ ተናግረዋል፡፡
የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ከስነ ልቦና ግንባታ ስልጠናው በተጨማሪም ለተፈታኝ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን መምሪያ ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡
የደብረታቦር ዩኒቨርሥቲ ፕሬዘዳት አነጋግረኝ ጋሸው /PHD/ በስልጠናው ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ተፈታኝ ተማሪዎች ቀሪ ጊዚያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ለፈተና መዘጋጀት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
አስተያዬታቸውን የሰጡ ተፈታኝ ተማሪዎች የሥነ-ልቦና ግንባታ ሥልጠናው ለፈተና በሚያደርጉት ዝግጅት ላይ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
See insights and ads
Promote
<img class=”x16dsc37″ role=”presentation” src=”data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:

4

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *