የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።
=======================
የግምገማ መድረኩ የዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ነው።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ በትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ በትምህርት ላይ ከህብረተሰቡና ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ሰፊ የምክክር መድረኮች ባለፈው ሩብ አመት በየአካባቢው መከናወናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም በትምህርት ለትውልድ ላይ ያልተወያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አጋር አካላትን ለመወያየት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የክልሉ ትምህርት ከመቸውም ጊዜ በላይ ፈተና ውስጥ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኃላፊው በዚህ አመት ለማስተማር ከታቀደው ሰባት ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን የተመዘገቡት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ትምህርትን ማቋረጥ የትውልድን የእድገት ሂደት ማቋረጥ መሆኑን ሁሉም አካል ተገንዝቦ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ መተባበርና የተመዘገቡ ተማሪዎችም በአግባቡ እየተማሩ ስለመሆኑ መከታተል እንደሚገባ ተገልጿል።
ከስድስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ የ2ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍት ወደ ክልሉ ገብቷል። ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጽሐፍት ህትመት እየተጠናቀቀ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤት የማጓጓዝ ሂደት ላይ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን