የወረታ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ
===========
ጥር 19/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የወረታ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ትምህርት ቤቱ አስታውቋል፡፡
የትምህርት ዘመኑን ትምህርት በወቅቱ የጀመረው የወረታ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከታህሳስ ወር ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በሁሉም ቀናት በተመረጡ ይዘቶችና መምህራን ልዩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሳምንቱን ሁሉንም ቀናት ተማሪዎች የቤተመጸሃፍት አገልግሎት እንዲያገኙ በመደረጉ ተማሪዎች የተሻለ እንዲዘጋጁ ያገዛቸው ሲሆን በቂ የስነለቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በባሉሙያዎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ከትምህርት ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከወላጆች ጋር ባለው የቅርብ ግኙነት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡና በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ልዩ የድጋፍና ክትትል መርሃ ግብር ቀርጾ እየሰራ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን



