መምህራን በአዲስ የተጀመሩትን የሙያና ተግባር ትምህርቶችን ለተማሪዎች በአግባቡ በማስተማር ትውልድን የማዳንና የማሻገር ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሙያና ተግባር ትምህርቶችን ለሚያስተምሩ መምህራን የማስተማር ስነ ዘዴን በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ማጠቃላያ ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ መምህራን በአዲስ የተጀመሩትን የሙያና ተግባር ትምህርቶችን ለተማሪዎች በአግባቡ በማስተማር ትውልድን የማዳንና የማሻገር ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በቀሰሙት የሙያና ተግባር ትምህርቶች እጆቻቸውን አፍታተው ራሳቸውን በአግባቡ የሚመሩና የሚያስተዳድሩ፣ ስራ ፈጣሪ፣ ቴክኖሎጅን የሚያፈልቁና በአግባቡ የሚጠቀሙ ፣ በስነምግባራቸው የተመሰገኑ እንዲሆኑ ለማስቻል የሙያና ተግባር ትምህርቶች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በማካተት ወደ ስራ መገባቱን አቶ ደምስ አመላክተዋል፡፡
በዚህ አመት ከ10 እስከ 12 የሚሆኑ የሙያና ተግባር ትምህርቶችን በክልላች ለመጀመር የሰው ኃይልና ግብዓት የማሟላት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿዋል፡፡ በቅጥርና በምደባ የሙያና ተግባር ትምህርቶችን እንዲያስተምሩ ኃላፊነት ለተሰጣቸው ከአንድ ሽህ አንድ መቶ በላይ መምህራን በሁለት ዙር የማስተዋወቂያ ስልጠናዎች መሰጠቱንና ቀጣይ በትምህርት ይዘቶቹ ላይ ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት መምህራንን የማብቃት ስራ እንደሚሰራ ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
አሚኮ
ያግኙን