በአሳታፊ የመማር ማስተማር ስነዘዴ አጋዥ መጽሐፍ ላይ ግምገማዊ ወርክሾፕ ተካሄደ።
ፖርትነርስ ኢን ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው አሳታፊ የመማር ማስተማር ስነዘዴ አጋዥ መጽሐፍ ላይ ግምገማዊ ወርክሾፕ ተካሂዷል።
የፖርትነርስ ኢን ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ ሪጅናል ማኔጀር አቶ አብዮት አሸናፊ መጽሐፉ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ስለ መማር ማስተማር ስነዘዴ እንዲረዱ፣
ስልጠና ሲሰጡ አጋዥ መጽሐፉ በማጣቀሻነት እንዲያገለግላቸው፣ እንዲሁም የመማር
ማስተማር ስነዘዴን በክፍል ውስጥ ሲተገብሩ እንዲጠቀሙበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ግምገማዊ ወርክሾፑ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ እየሩስ መንግስቱ መጽሐፉ መምህራን ብቃትን ተላብሰው የተማሪዎችን አቅምና ችሎታ ተረድተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ለማከናወን ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በመሆኑም እየተዘጋጀውን አሳታፊ የመማር ማስተማር ስነዘዴ አጋዥ መጽሐፍ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የመማር ማስተማር ስራ በክፍል ውስጥ ሲያከናውኑ እንዲጠቀሙበት ለማስቻል ቢሮው እንደሚሰራ ኃላፊዋ አመላክተዋል።
ፖርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ግንባታ፣ በአይን ጤናና ስነ ነጽህና ላይ አተኩሮ በክልላችን የላቀ አስተዋጽኦ እያከናወነ ያለ ድርጅት ነው።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
አሚኮ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን





See insights and ads
Boost
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:
115