ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ተቋቁመው ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ የሚገኙ መምህራንን እናመሰግናቸዋለን። አቶ ደምስ እንድሪያስ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
ለመምህራንና የትምህርት አመራሮች በስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለመምህራንና የትምህርት አመራሮች በስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የስልጠና ሂደቱን በአካል ተገኝተው የተመለከቱት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ተቋቁመው ትውልድን ለማሻገር ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ የሚገኙ መምህራንን አመስግነዋል ። የስነልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ ስልጠና ችግሮች በነበሩባቸው አካባቢዎች ለሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ስልጠናው መምህራን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶችን ተቋቁመው የማስተማርና ስራቸውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው በክልላችን በአምስት ማዕከላት ከ9 መቶ በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በመሰጠት ላይ ነው።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
አሚኮ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን