የአማራ ክልል የትምህርት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በንቅናቄ መድረኩ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይረጋ ሲሳይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ዛሬ የተገናኘነው ትውልድን ለማዳን ምክክር ለማድረግ ነው ብለዋል። የክልሉ የትምህርት ልማት በእጅጉ መጎዳቱን ገልጸዋል። የክልሉ የትምህርት ልማት ዘርፍ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ሌሎች አካባቢዎች በትምህርት የተቋደሱትን ውጤት ማግኘት አልቻልንም ነው ያሉት። የትምህርት ሥርዓቱ የሚያስገኘውን ጥቅም እያገኘን አይደለም ብለዋል። የባለፈውን ያላሳካን፣ የወደፊቱንም በጎ ነገር ያልጨበጥን ኾነናል ነው ያሉት።
በትምህርት ዘርፉ ያለንበትን ችግር መረዳት እና መፍትሔ ማስቀመጥ አለብን ብለዋል። ክልሉ በትምህርት ዘርፉ መሰናክል ውስጥ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በክልሉ ከፍተኛ የትምህርት ስብራት ገጥሟል ነው ያሉት። የትምህርት ስብራት እና መዘዙ በዚህ ዘመን ብቻ የሚታይ አይደለም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ዘላቂነት ያለው ጉዳትን የሚያስከትል ነው ብለዋል።
የረጅም ጊዜ ጉዳት በሚያስከትል ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን ነው ያሉት። መምህራን ሞራላቸው እና የማስተማር ፍላጎታቸው በብዙ መንገድ መጎዳቱንም ተናግረዋል። በርካታ መምህራን በሥነ ልቦና ጫና ውስጥ መኾናቸውን ነው የገለጹት። መማር የሚገባቸው ተማሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ብለዋል።
ሕጻናት ያልተገባ ኑሮ እየኖሩ ነው፣ ይሄም ማኅበረሰብን ወደ አልተገባ አቅጣጫ የሚወስደው ነው፣ እየደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ። ልጆች ሲሳደዱ ሲፈናቀሉ ማየት ልብ የሚሰብር ተግባር ኾኗል ነው ያሉት።
ትምህርት ቤቶችንም ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መኾናቸውን ገልጸዋል። የታጠቀው ኀይል ኾን ብሎ የአማራ ክልልን እና ኢትዮጵያን ለማዳከም ተልዕኮ ይዞ የሚሠራ ነው ብለዋል። ይህ ተግባር ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ መኾኑን ነው የተናገሩት።
ሕዝብን ለመጉዳት አልሞ የተነሳ ኀይልን ተልዕኮ የተቀበለ መኾኑን ነው የገለጹት። ወላጆች የትምህርት ዘርፉን መከላከል እና መጠበቅ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት መስጠት ካልተቻለ አደጋው ከፍ ያለ እንደሚኾንም ገልጸዋል።
አደጋውን በግልጽ ማሳየት እና መታገል ይገባል ነው ያሉት። ከዚህ ችግር ካልተሻገርን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ይደርስብናል ብለዋል። ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዳይኖር እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
መሪዎች እየደረሰ ያለውን ችግር በመረዳት የጋራ መግባባት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። በችግሩ እና በመፍትሔው ላይ የጋራ መግባባት በመያዝ መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። መሪዎች ተልዕኮዋቸውን በአግባቡ እንዲወጡም አሳስበዋል።
ክፍተቶችን እየለዩ፣ ለውጦችን እያሳዩ እንዲሠሩም አሳስበዋል። ትምህርት ሚኒስቴር እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።





+2
See insights and ads
Boost
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:
31