ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል
ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር)
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ቡድን የመስክ ድጋፍ ሪፖርት ግምገማ ተካሂደ(መጋቢት 23/2017 ትምህርት ቢሮ)
የማህበራዊ ዘርፍ የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ቡድኑም ከትምህርት፣ ጤና፣ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ፣ ወጣቶችና ስፖርት፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን በማህበራዊ ዘርፍ ስር ባሉ ተቋማት በ4 ከተማ አስተዳድሮችና 4 ዞኖች የመስክ ድጋፍ ሪፖርት አቅርቦ ተገምግሟል።
የድጋፍ ቡድኑ ሪፖርትም በዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም ቀበሌዎች የሰው ሀይል ስምሪቱ ያለበትን ደረጃ፣ የሴክተሮች ቅንጅታዊ አሰራር ምን አንደሚመስል፣ የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ በክልል ደረጃ የሚካሄዱ የልማትና መልካም አስተዳደር የንቅናቄ መድረኮች ቀበሌ ድረስ ስለመድረሳቸው፣ ዲጅታላይዜሽን ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በዝርዝር ቀርበው ተገምግመዋል።
በግምገማ መድረኩ ተገኝተው ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫ የሰጡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) የተቋማት ቁልፍ ተግባራት እንዲሳኩ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በ8 ዞኖች ያደረገውን የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ያመሰገኑት ዶ/ር ሙሉነሽ በራስ አቅም ችግር የመፍታት ልምድ ማዳበር ይገባል። የተቀመጡ አደረጃጀቶችን ማጠናከር፣ ዲጅታላይዜሽን ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን