መጋቢት 26/2017 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከዩኒስኮ ጋር በመተባበር ለመምህራን ትምህርት ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን በአእምሮ ጤና፣ ስነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ስልጠና በኮምቦልቻ ከተማ እየሰጠ ነው።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የመጭውን ትውልድ በአግባቡ የሚቀርጹ ብቁ መምህራንን ለማፍራት በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ከተቋቋሙበት ሶስት ዋና ዋና አላማዎች መካከል ብቁ መምህራንን ማፍራት አንዱ በመሆኑ አስልጣኝ መምህራንን በተቻለ መጠን ሙያዊ አበርክቷቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ደምስ አመላክተዋል።
መምህራን በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት አስከፊ በደሎች እና እንግልቶች እየደረሰባቸው መሆኑን የገለጹት ኃላፊው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመምህራን የማነቃቂያ ስልጠና እና ስርዓተ ትምህርት የማስተዋወቂያ መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *