መጋቢት 28/2017 /ትምህርት ቢሮ/ ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ከመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የቅድመ አንደኛ ትምህርትቤት በባሕርዳር ከተማ በሚገኘው መስከረም 16 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርትቤት ግቢ ውስጥ በአራት ወራት ጊዜ ገብቶ ለምጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ ትምህርትቤቱን የሚገነባ ኮንትራክተር ዛሬ በህዝብ ፊት ባካሄደው ጨረታ ለቷል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ፣ የባህርዳር ከተማ ትምህር መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ/ ዶክተር / የፓርትነር ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ይህዓለም አበበ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ ተማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ወላጆች በተገኙበት ትምህርት ቤቱን መገንባት የሚችለውን ተቋራጭ በጨረታ ለይቶ አሳውቋል፡፡ አሸናፊው ተቋራጭም በህዝብ ፊት የትምህርት ቤቱን ጥራት ጠብቆ ለመገንባት ቃል ገብቷል፡፡
በፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ / ዶክተር/ መስከረም 16 ትምህርትቤት የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ሳይሟሉለት በርካታ ሙህራን ሲያፈራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ትምህርትቤቱን ከነበረበት የመሰረተ ልማት ችግር ለማውጣት ከተማ አስተዳድሩ ከፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ እና ማህበረሰቡን በማስተባበር ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት ለመገንባት እሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል 26 ትምህርት ቤቶችን በመገንባት በትምህርት ዘርፉ የላቀ አስተዋጻኦ እያደረገ መሆኑን የድርጅቱ የአማራ ክልል አስተባባሪ አቶ አብዮት አሸናፊ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ የመምህራንን አቅም በማጎልበት በተማሪዎችና መምህራን ጤና፣ የትምህርት ቤት ግቢን በማስዋብ፣ በቴክኖሎጅና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ ደረጃቸውን ያላሟሉ ትምህርት ቤቶች በመደገፍ ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የመስከረም 16 የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ከተማ አስተዳደሩ ከፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ለመገንባት እያከናወነ ያለውን ተግባር በአድናቆት ገልጸዋል፡፡
ፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በትምህርት ቤት ግንባታ፣ የትምህርት ቤቶችን ግቢ አረንጓዴ በማድረግ፣ በተማሪዎችና መምህራን ጤና፣ በመምህራን ስልጠና በቴክኖሎጅ ዘርፍ እያደረገ ላለው ድጋፍና አስተዋጻኦ አቶ መኳንንት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የመንግስት ትምህርት ቤቶችን አቅም ማሳደግ የግል ትምህርትቤቶች ከሚጠይቁት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሚታደግ በመሆኑ ህብረተሰቡ ትምህርት ቤቶችን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የመስከረም 16 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጅ መምህር ህብረት ሰብሳቢ የሆኑት ሻለቃ አማረ ሲሳይ ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *