#education-for-generation
መምሪያው ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሙሉዓለም አቤ የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት በመንግስት፣ በህብረተሰቡና በአጋር አካላት ተሳትፎ 116 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ገጽታ መቀየር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ የትምህርት ተቋማት እንዲኖሩ ለማድረግ ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር በየጊዜው እየመከረ እየሰራ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታና የግብዓት ማሟላት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መምሪያ ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ልምድ የሚቀመርባቸው እንዲሆኑ ለማስቻል የተጀመሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።

#education-for-generation
ዶክተር ሙሉዓለም አቤ የባህር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ
የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶችን ምቹ ሳቢና ማራኪ በማድረግ የተማሪዎች ምገባ በማከናወን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎች ከህብረተሰቡና አጋር አካላት ጋር በመግባባት አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ መኳንንት ጥሪ አቅርበዋል።
በቀሪ ጊዜያት የከተማ አስተዳደሩ የ6ኛ፣ 8ኛና የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ማብቃት ላይ በትኩረት እንዲሰራ ኃላፊው አመላክተዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *