በትምህርት ለትውልድ ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር እየተገነባ ያለው በደሴ ከተማ የሆጤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታ 85 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ከሌሎች የክልልና የዞኖች የትምህርት አመራሮች ጋር በመሆን በትምህርት ለትውልድ ፕሮግራም በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እየተገነባ ያለውን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታ ጎብኝተዋል፡፡
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት በመልሶ ግንባታ ፕሮግራም ሐምሌ14/2014 ዓ.ም ነበር በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠው፡፡
ሁለት ብሎክ ባለ አንድ ወለል 12 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት በጌጤ አሰፋ ጠቅላላ ተቋራጭ እተገነባ ይገኛል፡፡
ይኸን ግንባታ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶክተር) ከሌሎች የክልልና የዞኖች የትምህርት አመራሮች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡
የግንባታው ተቋራጩ አቶ ጌጤ አሰፋ ግንባታው 85 በመቶ በላይ መድረሱን ገልፀው በቀጣይ ወር ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡
+4

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *