==========
ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የመረጃ አያያዝና በቴክኖሎጂ ጠቀሜታ ዙሪያ ለወረዳ ማኔጅመንት አባላት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ለሱፐርቫይዘሮችና ለዞን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የመምሪያው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኒዮሎጅ ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ አያሌው እንደገለፁት መረጃ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ሊጠፉ ስለሚችሉና አገልግሎት አሰጣጡን ከኋላ ቀር አሰራር በማላቀቅ መረጃን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ቴክኒዮሎጅን መሰረት ያደረገ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።
በዞኑ በ12 ወረዳዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ሌሎቹ ወረዳዎች በዳታ ቤዝ ተመዝግበው ይገኛሉ ብለው መረጃን በቀላሉ ለማገኘትና ለመያዝ፣ በጡረታ የሚገለሉ ባለሙያዎችን ለመለየት፣ የመምህራን ተማሪ ጥምርታ ለማወቅ የደረጃ እድገት ለመስራት የስራ ልምድ ለመስጠት ጠቀሜታ እንዳለው አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ተግባሩ በመምህራን፣ በርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘር በፍላጎታቸው ገንዘብ ከፍለው የጀመሩት በመሆኑ የዘመቻ ስራ ሆኖ እንዳይቀር የክልሉ መንግስት በባለቤትነት ይዞ የሚሰራ አካል በመመደብ ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ ወጥ የሆነ አሰራር እንድኖር ትኩረት ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና አበረታችና ለቀጣይ ስራ የሚየነሳሳና ከቴክኒዮሎጅ ጋር ይበልጥ እንድንተዋወቅ የሚያስችል ነው ብለው ተከታታይነት ያለው ስልጠና መሰጠት ቢቻል መልካም ነው ብለዋል።
ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
5.ቲክቶክ @amharaeducationbureau




