የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከወሎ ቀጠና የትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር ስራ አፈፃፀም ግምገማውን ከሚያዝያ 22_23/2017ዓ.ም በደሴ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ማጠቃለያም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሙሉ መልዕክቱም እንደሚከተለው ቀርቧል።
*****************

የትምህርት መዋቅሩ ባሳለፍናቸው ወራቶች ተሳትፎን በማረጋገጥ ረገድ ችግሮች ቢገጥሙትም ተማሪዎችን በማብቃት በኩል ግን ተሰፋ የሚሰጡ ሥራዎች ተሰርተዋል።

ከክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ እየተደረጉ ያሉ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች አበረታች እንደሆኑ ተገልፆል።

የት /ት ሸፋኑ አለመሳካቱ. በትውልዱ ላይ የሚፈጥረውን ክፍተት ተረድተን ሕብረተሰቡ ትምህርትን ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ እርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትምህርት ከየትኛውም ፖለቲካ ነፃ ነው። ትምህርት የየትኛውም ፖለቲካ ማስፈፀሚያ አጀንዳ መሆን የለበትም። ሊሆንም አይገባም። ይህንን ማህበረሰቡ ተረድቶ ከትምህርት ገበታ የራቁ ልጆቹ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ያለ መሠልቸት መስራት ይገባል ብለዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል፣ በአሁናዊ የሰላም ችግሮች ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ መገንባት፣ ግብአት ማሰባሰብ በተለይ አልማ የሚሰራቸው ሥራዎች ብዙዎቹ የትምህርት በመሆናቸው ለአልማ ስራ ስኬት ሁላችንም ድጋፍ ልናደርግ እንሚገባ አሳስበዋል።

ወጣቱ ትውልድ ቴክኖሎጅ እንዲጠቀም፣ በዚህም ስራ ፈጣሪ እንዲሆን በትምህርት ቤቶች የተጀመረውን ኢትዮ_ኮደርስ ስልጠና በትኩረት መከታተል ይገባል።

በቀሪ ወራት ሁሉንም ተማሪዎች ማብቃት ፤ በተለይ ክልል አቀፍና አገር አቀፍ ፈተና ላይ የሚቀመጡ የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት የድጋፍ ስራዎችን ማጠናከር፣

ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ መሠረት እንዲጠናቀቁ ክትትል ማድረግ፣

ለ2018 የትምህርት ዘመን አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከወዲሁ ማጠናቀቅ፣

የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ማስቀጠል፣

የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ዶ/ር ሙሉነሽ በማጠቃለያቸው አንስተዋል።