
እቅዱን በአግባቡ በመተግበር ያለፉ እድሎችን ማካካስ እንደሚገባ ተመላክቷል።
በአማራ ክልል የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የየተቋማቱ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የቀጣይ ሁለት ወራት እቅድ ትውውቅ መድረክም ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶክተር) በማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት በቀጣይ ሁለት ወራት እቅዳቸውን በአግባቡ በመተግበር ያለፉ እድሎችን ለማካካስ መስራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ ጤና ቢሮ፣ ሴቶች ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ወሳኝ ኩነት አገልግሎት በቀጣይ ሁለት ወራት የሚተገብሯቸውን እቅዶች ቀርበው ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
ግንቦት 10/2017
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation