በአማራ ክልል የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የየተቋማቱ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በግምገማ መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር)
በማህበራዊ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት እርስ በእርስ እየተናበቡ ህብረተሰቡን የማገልገል አቅም ማሳደግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት እየሰጡ የሚገኙትን አገልግሎቶች በተመለከተ አመራሮች በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ባካሄዱት የመስክ ምልከታ አስደናቂ አገልግሎቶች እየሰጡ የሚገኙ ተቋማት እንዳሉ መመልከታቸውን ኃላፊዋ አመላክተዋል።
ይሁን እንጅ በክልላችን ባጋጠመው ግጭት ምክንያት የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ተጎድተዋል። ያጋጠሙ ጉዳቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ ተቋማት በመተባበርና በመደማመጥ በጋራ አቅዶ መስራት እንደሚገባ ዶክተር ሙሉነሽ አስገንዝበዋል።
በስራችን ያመጣናቸውን ስኬቶች ለበለጠ መነሳሳት መጠቀም ይገባል በእንቅፋቶች ተስፋ መቁረጥ አይገባም ለውድቀትም ሆነ ለስኬታማነታችን ሁሉም ሰው ድርሻ እንዳለው በመገንዘብ የአመለካከትና ተሻጋሪ ለውጥ ለማምጣት የበለጠ መስራት ይገባል ብለዋል።
ተቋማትን ያለፉ ችግሮችን በመሻገር በአዲስ ርዕይ በመምራት የበለጠ ውጤት ማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ዶክተር ሙሉነሽ አመላክተዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation




