‎በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል” በሚል መሪ ቃል ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
‎በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሀዋ አደም እንደተናገሩት፦ ትምህርት የብዙ ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነትና ርብርብን የሚጠይቅ በመሆኑ ተቀናጅቶ በመስራት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
‎የአማራ ክልል የመሬት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ እብሬ ከበደ በበኩላቸው፦ ሃገርና ትዉልድን ማበልፀግ እና ማሻገር የሚቻለዉ የትምህርት አመራሩ እና ትምህርት ቤቶች የተጣለባቸዉን ኃላፊነት በአግባቡ ሲወጡ መሆኑን ተናግረዋል።
‎የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አህመድ፦ መምህራን የስልጠና፣ የግብዓት፣ የመኖሪያ ቤትና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች አሏቸው። እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
በትምህርት ዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የትምህርት ተቋማት፣ መምህራን እና ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው።
መረጃው የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *