የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ “ትውልድ በትምህርት ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል” በሚል መሪ ቃል ከወረዳ ከተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በውይይት መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ እንደገለፁት በትምህርት ስርዓቱ ያስመዘገብናቸውን ውጤቶችና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች እንዲሁም በዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የመምህራን ሚና ማመላከትና በቀጣይ ለሚሰጡ ሀገርና ክልል አቀፍ ፈተናዎች በውጤታማነት እንዲጠናቀቁ መምህራን የድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል የመድረኩ ዋና አላማ ነው ብለዋል።
የዞኑ ትምህርት መምርያ ኃላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ በበኩላቸው ምንም እንኳን በትምህርት ስርዓቱ ላይ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም መምህራን እነዚህን ችግሮች ተቋቁመው ትውልድን ለማሻገር ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
በመሆኑም በቀጣይ በሚሰጡ ፈተናዎች እንዳለፉት አመታት ሁሉ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መምህራን እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ትውልድ በትምህርት ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበልፅጋል የሚል የመወያያ ሰነድ በትምህርት መምርያው ኃላፊ ቀርቦ በተሳታፊዎች ወይይት ተደርጎበታል።
ከዚሁ በተጨማሪም በአሰራር ዙርያ ስለሚያጋጥሙ ጉዳዩች፣ ከመምህራን ጥቅማጥቅም እንዲሁም የኑሮ ውድነቱ በመመህራን ላይ ከፈጠረው ተፅዕኖ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በስፋት ቀርበው ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመድረኩ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ መምህራን፣ ርዕሰ መመህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና የኢትዮጵያ መመህራን ማህበር ሃላፊዎችና ባለሞያዎች ተገኝተዋል።
ግንቦት 11/2017
መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዘመቻ ን ኮሚዩኒኬሽን ን ነው