የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር “ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል ሀገር በትውልድ ይበለጽጋል” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

 

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በትምህርት የለማ አእምሮ ጠንካራ  ሀገር በመገንባት ለቀጣይ ትውልድ ማሻገር እንደሚችል ተናግረዋል። በመሆኑም መምህራን ትውልድ ላይ በመስራት እንደሀገር የተሻለ አስተዋጽኦ የማበርከት ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

 

ትምህርት ሴክተሩ በኮሮና፣ በሰሜን ጦርነትና በክልላችን ባጋጠመው የጸጥታ ችግር መጎዳቱን አመልክተዋል።

ከለውጡ በፊት ትምህርት ችግሮች ነበሩበት ከለውጡ ማግስት የትምህርት ስብራቶችን ለመጠገን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን  አቶ ሲሳይ ገልጸዋል። በቀጣይም የመምህራንን አቅም ለማጎልበትና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ መንግስት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

 

እንደ ሀገር ልጆቻችን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራንና የትምህርት አመራሩ እጅ ለእጅ ተያይዘው መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

 

የባህር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ /ዶክተር/ በ116 ሚሊዬን ብር በላይ ወጭ በማህበረሰቡ ተሳትፎ፣ በመንግስትና በአጋር አካላት በተገኘ ገቢ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከ9ሽህ 2 መቶ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። በዚህ ሁሉ ስራ መምህራን ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በርካታ ስራዎች መስራታቸውን አመላክተዋል።

በቀጣይ መምህራን ችግሮችን በጥናት በመለዬት ለመፍታትና የመፍትሄ አካል መሆን እንደሚገባ ሙሉዓለም አቤ /ዶክተር/ አስገንዝበዋል።

#AmharaEducationBureau

#ትምህርትለትውልድ

 

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

  1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
  2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
  3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
  4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

ያግኙን

  1. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
  2. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *