በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የቆየው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድና እድሳት እንደገና ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
=========
ግንቦት 14/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳትን አስመልክቶ ለዞንና ለክልል ባለሙያዎች የማነቃቂያ ስልጠና ዛሬ በባህርዳር ከተማ መስጠት ጀምሯል፡፡
በስልጠና መድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ የሙያ ፈቃድና እድሳት መምህራንና የትምህርት አመራሮችን ራሳቸውን እንዲያበቁና አቅማቸውን እንዲያሻሽሉ ያደረገና በሂደቱም የተማሪዎችን ውጤት እንዲሻሻል ምክንያት ነበር ብለዋል፡፡
የሙያ ፈቃድና እድሳት ለዘርፍ ምሁራን እና ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ያለው አበርክቶ የጎላ በመሆኑ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ልዩ ትኩርት ተሰጥቶት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው የሙያ ፈቃድና እድሳት መመሪያ፣የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድና በአዲሱ ስርዓተትምህርት የተዘጋጀውን የሙያፈቃድና እድሳት መመሪያ ዙሪያ ስልጠና እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ባለፉት አመታት በክልሉ በተሰራው ስራ ከ30ሺህ በላይ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች በፕሮግራሙ መሳተፋቸውም ታውቋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *