ስልጠናው የቢሮው ባለሙያዎችና የማኔጅመንት አባላት ትምህርት ቤት ሂደው ድጋፍና ክትትል ሲያደርጉ በትክክለኛ እውቀትና ክህሎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ ገልጸዋል።
ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መምህራን በስራ ላይ ስልጠና አቅማቸውን በማሳደግ ትምህርት ጥራት ለማሻሻል ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አቶ ደምስ ገልጸዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ /ዶክተር/መምህራንና የትምህርት አመራሩ ከደራሽና ወቅታዊ ስራዎች በመውጣት በእቅድ የተመራ ሙያዊ የሆነ ስራ ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መምህራን የአንዱን የእውቀት ክፍተት ሌላኛው እየሞላ ሙያዊ ብቃት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደሚረዳ ተናግረዋል። የትምህርት ባለሙያዎችም በትምህርት ተቋማት ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *