ከክልሉ መንግስት በተመደበ ከ3.9 ቢሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ በሰቆጣ፣ ደብረ ታቦርና ፍኖተ ሰላም ከተሞች ላይ እየተገነቡ የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ወቅታዊ የግንባታ ሁኔታን አስመልክቶ ከተቋራጮች፣ ከአማካሪ ድርጅቱና ከትምህርት ቢሮ መሀንዲሶች ጋር በጋራ ተገምግሟል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታዎቸ በታቀደላቸው ጊዜና በጥራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
የክልሉ መንግስት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጅ፣ በህክምና፣ በመሪነትና በሌሎች የሙያ ዘርፎች ዓለም አቀፍ ተወዳድሪ ተማሪዎችን ለማፍራት በማለም እያስገነባቸው የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተመደበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን አቶ መኳንንት ገልጸዋል።
የግንባታ ሂደታቸው በየ3 ወራት የሚገመገሙት ፕሮጀክቶቹ በግንባታ ወቅት የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመለየት ለመፍታት እንደሚያስችል ተገልጿል።
በጥቃቅን ምክንያቶች ግንባታ የሚያዘገዩ ተቋራጮች አፋጣኝ እርምት በመውሰድ ስራቸውን እንዲያቀላጥፉ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *