የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ እየሩስ መንግስቱ በቀጣይ ጊዜያት የሚሰጡ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን በውጤታማነት ለማከናወን ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በሚቀጥለው ወር ለሚሰጡት  የ6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል ፈተና  እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚወርድ ግብረ ሀይልና የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ  እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መምህራን ያልተሸፈኑ የትምህርት ክፍለጊዜዎችን ለተማሪዎች በመሸፈን፣ የመለማመጃ ጥያቄዎችን በመስራት፣ አንዳንድ አካባቢዎች የአዳር ጥናት ለተማሪዎች በማመቻቸትና ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ ቤተ መጽሐፍትን ክፍት በማድረግ ተማሪዎችን ለፈተና የማዘጋጀት ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ተማሪዎችና መምህራን አመቱን ሙሉ የለፉበትን ውጤት የሚያዩበት በመሆኑ ፈተናዎች የፈተና ህግና ስርዓት በጠበቀ መልኩ እንዲሰጡ ለማስቻል ወላጆች፣ የጸጥታ መዋቅሩ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ፣  የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት  በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ  ኃላፊዋ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

ከሰኔ 3 እስከ 4/2017 በሚሰጠው  የ6ኛ ክፍል ፈተና በ3,649  ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ከ154 ሽህ በላይ ተማሪዎች፡፡ ከሰኔ 5 እስከ 6/2017 በሚሰጠው  የ8ኛ ክፍል ፈተና በ2,728 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ከ148 ሽህ በላይ ተማሪዎችና ከሰኔ23 እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ድረስ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በ470 ትምህርትቤቶች የሚማሩ 99,498 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል፡፡

#AmharaEducationBureau

#ትምህርትለትውልድ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

  1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
  2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
  3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
  4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

ያግኙን

  1. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
  2. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *