የትምህርት ዘርፉን ማገዝ የልጆችን የወደፊት እጣ ፈንታ ማገዝ ነው።
ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር)
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ በትምህርት ዘርፉ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ከአጋር አካላት ጋር ምክክር መድረክ አካሂዷል።
በምክክር መድረኩም በአማራ ክልል የሰሜኑ ጦርነት ከተከሰተ እስካኹን ድረስ በትምህርቱ ዘርፍ ሰፊ ጉዳት አጋጥሟል።
ባለፋት ዓመታት በክልሉ በተካሄደ ግጭት ከ6ሺህ 154 በላይ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ ማለት በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች 57 በመቶዎቹ ትምህርት ቤቶች ለጉዳት ተዳርገዋል።
በተያዘው የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ይመጣሉ ተብሎ ከሚጠበቁ ተማሪዎች ውስጥ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎቸ ወደ ትምህርት ቤት አልገቡም።
ይህ የኾነው ደግሞ ከ4ሺህ 821 በላይ ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ምክንያት ባለመከፈታቸው ነው።
በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት የመማማሪያ ቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ተከስቷል።
በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ያጋጠመውን ጉዳት ለመቀነስ እና የትምህርቱን ዘርፍ ለማነቃቃት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በክልሉ ያለውን የትምህርት ዘርፍ ለማነቃቃት ድጋፍ አድራጊዎች እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በኩልም ድጋፍ እንዲደረግ ያሳሰቡት ዶክተር ሙሉነሽ ተማሪዎች በቤታቸው ኾነው በዲጂታል በመታገዝ መማር የሚችሉባቸው ኹኔታ እንዲፈጠሩ እገዛ ማድረግ እንደሚገባም አስታውቀዋል።
የትምህርት ዘርፉን ማገዝ የልጆችን የወደ ፊት እጣ ፈንታ ማገዝ በመኾኑ የተማሪዎች የትምህርት ጊዜ እንዳይባክን ሁሉም ትብብር ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ግጭቶች የልጆቻችንን የወደፊት እጣ ፈንታ ሊጎዳ አይገባም ብለዋል።
ተማሪዎችን እና ትምህርት ቤቶችን ማገዝ የሀገርን መፃኢ ዕድል ማገዝ በመኾኑ መንግሥታዊም ኾኑ መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ትምህርት ቤቶችን በማገዝ እና መልሶ በመገንባት ሊተባበሩ እንደሚገባም አስታውቀዋል።
ግንቦት 21/2017





+3
See insights and ads
Boost post
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:
72