ግንቦት 22/2017(ደብረብርሐን)- የደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ በ68 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ባለ ሁለት ወለል ህንፃ የፌደራል፣ የክልል፣ የሰሜን ሸዋና ደብረብርሐን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሐመድ(ዶ.ር)፣ የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ፣ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም መሐመድ(ዶ.ር)፣ የክልል፣ ደብረብርሐን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ ዞን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
5.ቲክቶክ @amharaeducationbureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *