ግንቦት 25/2017 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ ከግንቦት 22 እስከ 25/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ቀናት “ፈጠራ ለሁለተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎችና መምህራን ክልላዊ የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይ የማጠቃላያ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በማጠቃላያ መርሀ ግብሩ ላይ በፈጠራ ስራቸው ተወዳድረው አሸናፊ ለሆኑ መምህራንና ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።
በእውቅናና ሽልማት አሰጣጥ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ/ዶክተር/ የአገራችን ልማት፣ ኢኮኖሚ ፣ሳይንስ፣ ቴክኖሎጅ፣ ባህልና እሴት ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
የፈጠራ ስራ ላይ ለሚሰማሩ መምህራንና ተማሪዎች የተመቻቸ ከባባቢ ለመፍጠር የአማራ ክልል ትሞህርት ቢሮ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የአማራ ክልል ሳይንስና ኢኖቬሽን ቢሮ ኃላፊ አቤል ፈለቀ ሳይንስና ፈጠራ ማህበረሰባዊ መሰረት እንዲኖረው ለማስቻል እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ ጀኔሬተር ሰርቶ ያቀረበው የኮምቦልቻ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተምኪን መሐመድ በ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ዘርፍ ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የላፕቶፕ ኮምፒውተር እና የ16 ሽህ ብር ተሸላሚ በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ገልጾ እንዲህ አይነት የፈጠራ ስራ ውድድሮች ተማሪዎችና መምህራን የሚያበረታታ መሆኑን ተናግሯል። ሽልማቱ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት የበለጠ እንደሚያግዘው ገልጿል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *